ከታሪካዊው የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ጀርባ ያሉ ያልተነገሩ እውነታዎች

የስፔን ተጫዋቾች ሚኬል ኦያርዛባል፣ አሌክስ ባኤና እና ዳኒ ኦልሞ በሐምሌ 10 ቀን በሎስ አንጀለስ፣ አሜሪካ ከቤልጂየም ጋር ባደረጉት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ፍፁም ቅጣት ምት ከመምታታቸው በፊት በቅርበት ሲነጋገሩ ይታያሉ።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ከአርጀንቲና ጋር ለዋንጫ የሚጋጠሙት የስፔን ተጫዋቾች
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 4 ደቂቃ

የ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያው ኳስ ከመመታቱ በፊትም አንዳንድ ታሪካዊ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።

ይህ የዓለም ዋንጫ ከሁለት በላይ አገራት ያስተናገዱት ብቸኛው ውድድር ሲሆን፣ 48 አገራት በመሳተፋቸው ክብረ ወሰን የሆነ ውድድር ነው።

ዛሬ እሁድ ከሚካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ በፊት በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በሜክሲኮ በሜዳ ውስጥ እና ከሜዳ ውጪ ስለተከናወኑት ነገሮች ብዙም የማይታወቁት ክስተቶች እና ቁጥሮች የትኞቹ ናቸው?

ሊያስደንቅዎት የሚችሉ የውድድሩን አንዳንድ እውነታዎች እና ቁጥሮች እነሆ።

ስስታሞቹ ፈረንሳዮች እና ስፔናውያን

የአርጀንቲና ግብ ጠባቂ ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, የአርጀንቲና ግብ ጠባቂ ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ

ስፔን በግማሽ ፍፃሜው ፈረንሳይ ለሦስተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ለማንሳት የነበራትን ፍላጎት አኮላሽታለች።

ነገር ግን ሁለቱም ቡድኖች ከፍፃሜው በፊት ባሉት ሰባት ጨዋታዎች 120 የግብ ሙከራዎችን አድርገዋል።

ዕድለ ቢሷ እንግሊዝ

በግማሽ ፍፃሜው የዋንጫ ህልሙ የተገታው ቡድን እንግሊዝ ነው። በዚህ የዓለም ዋንጫ ላይ በጣም ዕድለ ቢሱ ቡድን ሲሆን 102 ጥፋቶች (ፋውል) ተሰርተውበታል።

ለፍጻሜ ጨዋታ የተጋጠሙት እንግሊዝ እና የአርጀንቲና ተጫዋቾች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ለፍጻሜ ጨዋታ የተጋጠሙት እንግሊዝ እና የአርጀንቲና ተጫዋቾች

የቡድኑ አንቀሳቃሽ ሮድሪ

የስፔን አማካይ ተጫዋች ጥሩ ለውጥ አድርጓል፤ በሰባት ጨዋታዎች ወደ 84 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ርቀት ተጉዟል።

የፈረንሳዩ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ ሐምሌ 9 ቀን በቦስተን ፈረንሳይ ሞሮኮን ባሸነፈችበት ጨዋታ ጎል ያስቆጠረ ሲሆን ሞሮካዊው ግብ ጠባቂ ቦኑ ከበስተጀርባ ሆኖ እጆቹን ዘርግቶ ይታያል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ኪሊያን ምባፔ በ2026 የዓለም ዋንጫ ፈጣኑን ሩጫ አስመዝግቧል

ተወንጫፊው ምባፔ

የፈረንሳዩ ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች በዚህ ውድድር ላይ ፈጣኑ ተጫዋች ሲሆን፣ በሩብ ፍፃሜው ሞሮኮን ባሸነፉበት ወቅት በሰዓት 37.6 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ሸፍኗል።

ሌላኛው ተጫዋች ስዊድናዊው አንቶኒ ኤላንጋ ብቻ 37 ኪሎ ሜትር በሰዓት መሮጥ በመቻል ተቀራራቢ ሰዓት አስመዝግቧል።

የኩራካኦ ግብ ጠባቂ ኤሎይ ሩም ቡድኑ ከኢኳዶር ጋር ባደረገው ጨዋታ ኳሱን ለማዳን ሲወረወር

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ኤሎይ ሩም በአንድ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በመደበኛ ጊዜ ከፍተኛውን ኳሶች አድኗል

የፓራጓይ ተከላካይ እና የኪዩራሳው ክብረ ወሰን

ፓራጓይ በውድድሩ ላይ ከታዩት ታላላቅ ክስተቶች አንዱን አስመዝግባለች፤ የአራት ጊዜ የሻምፒዮናነት ክብር የነበራት ጀርመንን በ32ኛው ዙር በማሸነፍ፣ በጥሎ ማለፍ ዙር ደግሞ ተወዳጇን ፈረንሳይን ለ70 ደቂቃዎች በመገዳደር ታሪክ ሠርታለች።

ግብ ጠባቂው ኦርላንዶ ጊል በስድስት ጨዋታዎች 28 ኳሶችን በማዳን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ይህም የውድድሩ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

የኪዩራሳው ግብ ጠባቂ ኤሎይ ሩም በአንድ ጨዋታ 15 ኳሶችን በማዳን ስሙ በክብር የሚጠቀስ ሌላኛው በረኛ ነው።

ብሔራዊ ቡድኑ ከኢኳዶር ጋር ባደረገው ጨዋታ ግብ ሳይቆጠርበት በመደበኛው ሰዓት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኳሶች በማዳን ክብረ ወሰኑን ተረክቧል።

የባከኑ ፍጹም ቅጣት ምቶች

በዚህ የዓለም ዋንጫ በርካታ የፍጹም ቅጣት ምቶች ተሰጥተዋል። ቁጥሩን በትክክል ለማስቀመጥ 61 ፍጼም ቅጣት ምቶች የተሰጡበት የዓለም ዋንጫ ነው።

ነገር ግን ኳስ ከመረብ የተዋሃደው በ41ዱ ብቻ ነው። ፊርም ኦፕታ የተባለው የስፖርት ተንታኝ በአውሮፓውያኑ 1966 ከተካሄደው ግጥሚያ ወዲህ ዝቅተኛ ዒላማውን የጠበቀ የቅጣት ምት የታየበት ነው ብሏል።

በዚህ ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ ከአንዴም ሁለቴ ፍጹም ቅጣት ምት ስቷል።

በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ተሰቅሎ የሚታይ የዓለም ዋንጫ ባነር እና የሚበር አውሮፕላን

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በዚህ የዓለም ዋንጫ በርካታ የአውሮፕላን በረራዎች በመካሄዳቸው የአየር ብክለት እንደሚጨምር ያምናሉ

በርካታ ተጋጣሚዎች እና በካይ ጋዝ

የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ባለሙያዎች ኔትወርክ የሆነው 'ሳይንቲስትስ ፎር ግሎባል ሪሊፊኬሽን' (ኤስጂአር) በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የአየር ብክለት እንደሚኖር ይገምታል።

ባለፈው ዓመት በወጣው ሪፖርት ላይ ባለሙያዎቹ የውድድሩ የበካይ ጋዝ ልቀት ዘጠኝ ሚሊዮን ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል፤ ይህም ካለፉት አራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች አማካይ በእጥፍ የሚበልጥ ነው።

ከፍተኛ ተመልካች የታደማቸው ጨዋታዎች

እንደ ፊፋ መረጃ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር በመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ውድድር ላይ ከፍተኛ የተመልካቾችን ቁጥር አስመዝግቧል።

4.6 ሚሊዮን ሰዎች በ72 ጨዋታዎች ላይ መገኘት ችለዋል። ይህም በአውሮፓውያኑ 1994ቱ በአሜሪካ አስተናጋጅነት በተካሄደው ውድድር የተመዘገበውን ቁጥር የሚበልጥ ነው።

በ16ቱ ዙር መጨረሻ ላይ የተመልካቾች ቁጥር ወደ 6.25 ሚሊዮን ከፍ ብሏል። ይህም ከኬፕ ቬርዴ ሕዝብ ብዛት በ12 እጥፍ ይበልጣል።

የኬፕ ቨርዴ ግብ ጠባቂ ቮዚንሃ በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ወቅት ከሜዳ ሲወጣ ከደጋፊዎቹ ጋር ሰልፊ እየተነሳ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ከአሁን ጀምሮ ቮዚንሃ ሰልፊ ለመነሳት ምናልባት ብዙ ጊዜ መቆም ይኖርባታል

ቮዚንሃ፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ክስተት

ስለ አፍሪካዊቷ ደሴት ኬፕ ቬርዲ እና የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ተጫዋቾች ሲነሳ የግብ ጠባቂው ቮዚንሃ ጀግንነት ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያነት ተቀይሯል።

ወደ ዓለም ዋንጫ ሲመጣ 50 ሺህ የኢንስታግራም ተከታዮች ብቻ የነበሩት ግብ ጠባቂው የዓለም ዋንጫ በተካሄደባቸው ቀናት ውስጥ የተከታዮቹ ቁጥር ከ29 ሚሊዮን በላይ መድረሱን የገጹ መረጃ ያሳያል።

የፊላደልፊያ ከፍተኛ ሙቀት

በሰሜን አሜሪካ ያለው ከፍተኛ ሙቀት መጠን እየጨመረ በሄደበት ጊዜ ፊፋ በ2026 የዓለም ዋንጫ አስገዳጅ ፈሳሽ ለመውሰድ ፋታ የሚያገኙበት ጊዜ እንዲሰጣቸው የሚያደርግ አሠራር ጀምሯል።

ያም ሆኖ የፈረንሳይ እና የፓራጓይ ተጫዋቾች በፊላደልፊያ ስታዲየም ባካሄዱት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 38 ዲግሪ ሴልሺየስ የደረሰውን ሙቀት መቋቋም ነበረባቸው። ይህም እስካሁን ድረስ ያለ አየር ማቀዝቀዣ የተካሄደው ሞቃታማው ጨዋታ ነው።

ሊዮኔል ሜሲ እና ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, እሁድ ዕለት ሜሲ እና ትራምፕ ዳግም ይገናኙ ይሆን

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያልታዩበት ውድድር

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአገራቸው አጥቂ ፎላሪን ባሎገን የተሰጠው ቀይ ካርድ እንዲሰርዝ ፊፋን በተሳካ ሁኔታ ማግባባት እንደቻሉ ከተናገሩ በኋላ ውዝግብ ተፈጥሯል።

ሆኖም ትራምፕ እስካሁን ድረስ በውድድሩ አንድም ጨዋታ ላይ አልተገኙም።

ይህም በአስተናጋጅ አገር መሪ ዘንድ ያልተለመደ ነው። ሆኖም ግን፣ በፍጻሜው ጨዋታ ላይ እንደሚገኙ እና ዋንጫውን ለአሸናፊው ቡድን አንበል እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል፤ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንታኖም ይህንኑ ተናግረዋል።