BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
ቀጥታ, አሜሪካ የኃይል ተቋማቷን ካጠቃች ሁቲዎች የቀይ ባሕር የነዳጅ መተላለፊያን ለመዝጋት እንዲዘጋጁ ኢራን ማሳሰቧ ተዘገበ
አሜሪካ የኢራን የኃይል ማመንጫ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ፤ የየመን ሁቲ አማጺያን በቀይ ባሕር የሚገኙ የነዳጅ መተላለፊያን ለመዝጋት እንዲዘጋጁ ቴህራን ማሳሰቧን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ። የኢራን ወዳጅ የሆኑት የሁቲ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም በቀይ ባሕር በኩል በሚያልፉ መርከቦች ላይ ጥቃት በመፈጸም የባሕር ላይ እንቅስቃሴን አስተጓጉለው ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በተጀመረው ሀገራዊ ምክክር የመጨረሻ ጉባኤ መክፈቻ ላይ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ። ከአራት ዓመታት በላይ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ አጀንዳ ሲያሰባስብ እና ተወያዮችን ሲያስመርጥ የቆየው ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን የመጨረሻውን ምክክር የሚያደርግበትን ጉባኤ ዛሬ ረብዑ ሐምሌ 8 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ ተጀምሯል።
አራት ሺህዎቹ የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች በአጀንዳዎች ላይ የሚወያዩት እንዴት ነው?
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአራት ዓመት በላይ ከወሰደ የተወካዮች መረጣ፣ አጀንዳ ማሰባሰብ እና ሌሎች ተግባራት በኋላ ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም. የመጨረሻውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ያስጀምራል። በአዲስ አበባ ከተማ 'አዲስ ኮንቬንሽን ሴንተር' በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ ክልሎች፣ ወረዳዎች፣ ከፌደራል እንዲሁም በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተወጣጡ ከአራት ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የዓለም ዋንጫ - 2026
አዳዲስ ታሪክ የሚመዘገብበት 23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሙሉ መረጃን እዚህ ያገኛሉ
የዓለማችን ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር የዓለም ዋንጫ በ23ኛ ዙር ውድድር በርካታ አዳዲስ ነገሮች የሚታዩበት ሆኖ ከሰኔ 4 አስከ ሐምሌ 12 ድረስ ይካሄዳል። በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አገራት ውስጥ የሚካሄደውን የዓለም ዋንጫ ተጎራባቾቹ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ያስተናግዱታል። የውድድር ቦታዎች፣ ቀናት፣ ሰዓታት፣ ውጤቶች፣ የምድብ ድልድል እና ደረጃ እንዲሁም ሌሎች የጨዋታ ዝርዝር መረሃ ግበሮች እዚህ ይቀርባሉ።
በዓለም ዋንጫ አስሩ ምርጥ የብሔራዊ ቡድኖች ማሊያዎች የትኞቹ ናቸው? ዝነኛ ያደረጋቸው ምንድን ነው?
የዓለም ዋንጫ ምርጥ ማሊያዎች የትኞቹ ናቸው? ምንድን ነው ዝነኛ ያደረጋቸው? ቢቢሲ ስፖርት የምንጊዜም ተወዳጅ 10 ማሊያዎችን በደረጃ አስቀምጧል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለምርጫ፤ ስለፕሪቶሪያ፤ ስለአርሲ. . . ምን አሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰናባቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተዋል። ቢቢሲ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ውስጥ አምስት ዋና ዋና ጉዳዮችን መርጦ አውጥቷል።
የዊግ እና 'ሂውማን ሄር' ከጡት ካንሰር ጋር የሚገናኙ ኬሚካሎች
ፀጉር ላይ የሚቀጠለው ዊግ እና ሂውማን ሄር ከጡት ካንሰር፣ ከሆርሞን መዛባት እንዲሁም በሥነ ተዋልዶ ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ኬሚካሎችን መያዛቸውን ጥናቶች አሳዩ። ሳይንቲስቶች ዊጎቹ ላይ 50 ጎጂ ኬሚካሎችን አግኝተዋል። እነዚህ ኬሚካሎች ፀጉር ላይ የሚቀጠሉ፣ የሚጠለቁ እንዲሁም የሚሰፉ ዊጎች እና ሂውማን ሄር ላይ ይገኛሉ።
ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የሚፎካከሩት ዕጩዎች
በዘንድሮው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል ጎማ 2 ምርጫ ክልል ይወዳደራሉ። እርሳቸውን ለማሸነፍ የሌሎች ፓርቲ ዕጩዎችም ይፎካከራሉ። እነዚህ እጩዎች ከአሁን በፊትም ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የተወዳደሩ ናቸው?
ቪዲዮ, የኢትዮጵያ እና የሱዳን መካሰስ እና ፍጥጫ
ለረጅም ጊዜ ወዳጅ ሆነው የቆዩት ጎረቤታሞቹ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነታቸው ሻክሯል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በይፋ በመውጣት ከመካሰስ አልፈው ወደ ግጭት የሚያመሩ ዛቻዎች እየተሰሙ ነው። ለመሆኑ ሁለቱ ጎረቤታሞችን እዚህ ያደረሳቸው ምንድን ነው?
አነጋጋሪ ጉዳይ
የተወሰኑ የአፍሪካ አገራት ለምን ኢትዮጵያ የፈረመችውን የትራምፕ የእርዳታ ስምምነት ውድቅ አደረጉ?
አሜሪካ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋሟን ከዘጋች በኋላ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ በኩል አዲስ ዓለም አቀፍ የጤና ስትራቴጂ ዘርግታለች። በዚህ አሰራር ድጋፍ የሚያገኙ መንግሥታት እንደ የጤና መረጃዎችን ለአሜሪካ ማጋራት ያሉ ኃላፊነቶች ተጥሎባቸዋል። አገራት እና ተቋማት አሰራሩ ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። ለምን?
ከጠ/ሚ ዐቢይ የ"አብረን እንሥራ" ጥያቄ የቀረበላቸው ዶ/ር ደሳለኝ ከፖለቲካ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ከመንግሥታቸው ጋር አብረው እንዲሠሩ ጥሪ ያቀረቡላቸው ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ራሳቸውን ከፖለቲካ ማግለላቸውን አስታወቁ። ደሳለኝ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእንደራሴነት ያሳለፏቸውን አምስት ዓመታት "አስቸጋሪ እና ፈታኝ" ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
"ህወሓትም ጭምር ቀልብ ከገዛ. . . ለመነጋገር ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል" ጠ/ሚ ዐቢይ
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕዝብ እንደራሴዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ህወሓትም ጭምር ቀልብ ከገዛ. . . ለመነጋገር ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል" አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በምርጫ ቦርድ ሕጋዊ እውቅናው የተሰረዘበት ህወሓት የተግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ካስወገደ በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ባለበት ጊዜ ነው።
ሂውማን ራይትስ ዎች በትግራይ ክልል "እስከ 15 ዓመት የሆኑ ልጆች" በግዳጅ ተመልምለዋል ሲል ከሰሰ
በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው "እስከ 15 የሆኑ ልጆች" ጭምር "እየታፈኑ እና በሕገ ወጥ መንገድ እየተመለመሉ" መሆኑን ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች 'ሂውማት ራይትስ ዎች' ገለጸ። ተቋሙ፤ አሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ እና የአፍሪካ ኅብረቶች "የትግራይ ባለሥልጣናት የግዳጅ ምልመላውን እንዲያቋርጡ እና የተያዙ ልጆችን በሙሉ እንዲለቅቁ" የሚያስችል ጫና እንዲያደርጉ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደሚከስሱ ሲናገሩ የነበሩት የቦንድ አበዳሪዎች እንዴት ከስምምነት ደረሱ?
ከአንድ ወር በፊት ለኢትዮጵያ ገንዘብ ያበደሩ ባለሀብቶች የአገሪቱን መንግሥት እንደሚከስሱ አስታውቀው ነበር። ትናንት ሰኞ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም. ግን የገንዘብ ሚኒስቴር ከባለሀብቶቹ ጋር የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት መደረሱን አስታውቋል።
የኤርትራ መንግሥት ዜጎች በእጃቸው ያለ ገንዘብን በአንድ ወር ወደ ባንክ እንዲያስገቡ አዘዘ
የኤርትራ መንግሥት ዜጎቹ በእጃቸው ላይ ያለ ገንዘብን በሙሉ እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ ወደ ባንክ እንዲያስገቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ አወጣ። የኤርትራ ማዕከላዊ ባንክ ማክሰኞ ዕለት ባወጣው ጥብቅ ማሳሰቢያ፤ በአገሪቱ ውስጥ በግለሰቦች እና በተቋማት እጅ የሚገኝ የአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ (ናቅፋ) በሙሉ ዛሬ የጀመረው የአውሮፓውያን ሐምሌ ወር መጠናቀቂያ ድረስ ወደ ባንክ እንዲገባ አዝዟል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ሆሳዕና ከተማ 400 ገደማ ውሾች ለምን እና እንዴት ተገደሉ?
ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ውሾች በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳዩ ምሥሎች በማኅበራዊ ሚዲያ ከተጋሩ በኋላ በርካቶችን አስቆጥቷል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ነዋሪዎች እና የከተማዋ ባለሥልጣን እንዳሉት ውሾቹን በጅምላ መግደል የተጀመረው ሦስት ታዳጊዎች ከእብድ ውሻ በሽታ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ነው።
በኢትዮጵያ የተከፈተው የመጀመሪያው የእናት ጡት ወተት ባንክ የሚሰጠው አገልግሎት ምንድን ነው?
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነ የእናት ጡት ወተት ባንክ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ተከፈተ። ባንኩ ከለጋሽ እናቶች የተሰበሰበ ወተት የደኅንነት ሂደቶችን አልፎ የሚጠራቀምበት ሲሆን፣ ወተቱ በተለያየ ምክንያት ከእናቶቸቻው የጡት ወተት ማግኘት ለማይችሉ ጨቅላ ሕፃናት ያቀርባል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
የአሜሪካ እና ኢራን ጦርነትን ያስቆማል የተባለው ስምምነት ምን ምን ይዟል?
የአሜሪካ እና ኢራን ከመግባባት ላይ የደረሱበት ሰነድ ይፋ ሆኗል። ስምምነቱ የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት እንደሚያደርግ እንዲሁም ለወራት የቆየውን ጦርነት ያስቆማል የሚል እምነት አሳድረዋል። ትራምፕ ባለ 14 ነጥቡ ስምምነት "በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ" መሆኑን እና ኢራን ልትጠቀም የምትችለው ስምምነቱን የምታከብር ከሆነ ብቻ ነው ብለዋል። የስምምነቱ ነጥቦች ምን ምን ይዘዋል?
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የአሜሪካንን ባሕር ኃይል እየፈተኑ ያሉት የኢራን ትናንሽ ጀልባዎች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ባሕር ኃይል እንዳወደሙ ቢናገሩም፣ ኢራን ትናንሽ ፈጣን ጀልባዎችን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦችን እንቅስቃሴን መግታት ችላለች። ስለእነዚህ ውጤታማ የኢራን ፈጣን ወታደራዊ ጀልባዎች ምን እናውያለን?
አሜሪካ እና ኢራን ድል እንደተቀዳጁ እያወጁ ባሉበት ጦርነት አሸናፊው ማን ነው?
አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገውን ጦርነት ማቆሟን እየተናገረች ነው። በሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም ከተደረገ ከሳምንታት በኋላ ማክሰኞ ዕለት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ "ኢፒክ ፊውሪ' በማለት የተጠራው ዘመቻ ማብቃቱን ተናግረዋል።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በተደረገው ጦርነት ማን አሸነፈ?
ከየፈርጁ
በድምጻውያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ኤአይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ መልክ እንዴት ሊለውጠው ይችላል?
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ተገርበው በአዲስ መልክ የተሠሩ ሙዚቃዎች የዩቲዩብ ገፆችን ወርረዋል። የአንጋፋ እና ተወዳጅ ድምጻውያን የሙዚቃ ሥራዎች አማርኛው በተኮላተፈ የኤአይ አንደበት እየተዘፈኑ ነው። አንዳንዶቹ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዕይታዎች አሏቸው። የአድማጭን ትኩረት የሳቡም ይመስላሉ። ለመሆኑ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ልህቀት በተለይ በሙዚቃው ዘርፍ ምን ያሳጣ፣ ምን ያስገኝ ይሆን? የኢትዮጵያን ሙዚቃስ በምን መልኩ ሊለውጠው ይችላል?
የአሜሪካዋ ግዛት ምክር ቤት ለአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ሰየመ
በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት 2' በግዛቱ የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን እንዲሆን የቀረበን የውሳኔ ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ አፀደቀ። ይህ 'ኤችአር 441' የተሰኘው የውሳኔ ሐሳብ የፀደቀው ባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ነው።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለምን ስለ እናታቸው በአደባባይ አይናገሩም?
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪን ጆንግ ኡን በምሥጢር ከያዟቸው ነገሮች አንዱ የእናታቸው ጉዳይ ነው። ለ15 ዓመታት በሥልጣን ሲቆዩ አንድም ቀን የእናታቸውን ስም በአደባባይ አንስተው አያውቁም። ይህ ለምን ሆነ?
የተመለሱ ጥያቄዎች
ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል። የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው። አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ሁለቱም ወጣቶች ከራሳቸው ህመም ተነስተው ሕክምና ለማጥናት መወሰናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች ማራቶንን ከሁለት ሰዓት ባነሰ ጊዜ እንዲጨርሱ ያስቻላቸው ምስጢር ምንድን ነው?
ትናንት እሁድ በለንደን የተካሄደው የማራቶን ውድድር ኬንያዊው ሳባስቲያን ሳዌ እና ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻ ከሁለት ሰዓት በታች ተከታትለው በመግባት ዓለምን አስደምመዋል።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!















































































































