ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አርቴታ ወደ ፒኤስጂ? ፒክፈርድ ወደ ዩናይትድ?ቼልሲስ ስንት ተጫዋቾችን ሊያስፈርም ቋምጧል?
የፈረንሳዩ ክለብ ፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን የአርሰናሉን አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ ወደ ፓሪስ ለማምጣት በማቀድ ማናገሩ ተሰምቷል።
ፒኤስጂ የቀድሞውን የባየርን ሙኒክ አሠልጣኝ ጁሊያን ናግልስማን ለማስፈረም ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
አሠልጣኝ ፍለጋ ላይ ያለው ፒኤስጂ ሉዊስ ኤንሪኬ፣ ዣቪ አሎንሶ እና ቲያጎ ሞታን በዕጩነት ይዟል። ክለቡ አርቴታን ለመቅጠር አሰልጣኙን ያናግር እንጂ ብዙ ሊሳካላት እንደማይችል ይረዳል ብሏል አርኤምሲ።
ማንቸስተር ዩናይትድ የ29 ዓመቱን እንግሊዛዊ ግብ ጠባቂ ከኤቨርተን ለማስመጣት ዋጋ ማቅረባቸውን ስታር ሰንደይ ዘግቧል።
ዩናይትድ ለጆርዳን ፒክፈርድ ያቀረበው ዋጋ 45 ሚሊዮን ፓውንድ መሆኑ ተሰምቷል።
ከፒክፈርድ በተጨማሪ ከቼልሲ ሜሰን ማውንትን ለማስመጣት እየሞከሩ ያሉት ዩናይትዶች ለማውንት ያቀረቡትን ዋጋ ከ40 ወደ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍ ማድረጋቸውን ሜል አስነብቧል።
ቼልሲ በበኩሉ የኢንተር ሚላኑን ኒኮሎ ባሬላ በሮሜሉ ሉካኩ ለመለወጥ ማሰቡን የጣሊያኑ ኮሪዬሬ ድሎ ስፖርት ጋዜጣ ፅፏል።
የ26 ዓመቱ ጣሊያናዊ ኒኮሎ ባሬላ ወደ እንግሊዝ የሚመጣ ከሆነ በውሰት ወደ ኢንተር የሄደው ቤልጂየማዊው ሮሜሉ ሉካኩ ጣሊያን ይቀራል።
ኒውካስል ዩናይትድ የቼልሲው የግራ መስመር ተመላላሽ ስፔናዊው ማርክ ኩኩሬያን በያዝነው የክረምት መስኮት ለማስፈረም ማቀዱን የዘገበው ሰንደይ ሚረር ነው።
ቼልሲ፤ የ23 ዓመቱን እንግሊዛዊ ኮነር ጋላገር ለብራይተን ሰጥቶ ኤኳዶራዊውን አማካይ ሞይሰስ ካይሴዶ ሊያስፈርም ይችላል ይላል ሚረር።
በርካታ ተጫዋቾችን ለማሰፈረም ያቀደ የሚመስለው ቼልሲ የሴልታ ቪጎውን የ21 ዓመቱ ስፔናዊ ጋብሪ ቬይጋን ለማስፈረም ከሊቨርፑል ጋር ፉክክር ውስጥ ገብቷል።
የ31 ዓመቱ የቼልሲ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ወደ ሳዑዲ አራቢያው አል ሂላል ሊሄድ ይችላል ሲል ፋብሪዚዮ ሮማኖ ፅፏል።
ሮማኖ እንደሚለው ከሆነ አል-ሂላል ከሴኔጋላዊው ተከላካይ ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል።
የስፔኑ ሙንዶ ዲፖርቲቮ እንደሚለው ከሆነ ቼልሲ፤ ፒዬር ኤሜሪክ ኦባሚያንግ፣ ሃኪም ዚዬች እና ግብ ጠባቂው ሜንዲን ለሳዑዲ ክለቦች ለመሸጥ አቅዷል።
የብሬንትፈርዱ የ27 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ከቶተንሃም ጋር በግል ስምምነት ላይ እንደደረሰ ፍብሪዚዮ ሮማኖ ጠቁሟል።
በውሰት ከማርሴ ጋር የከረመው አይቮሪ ኮስታዊው ኤሪክ ባይ ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ስፔኑ ሪያል ቤቲስ ሊያመራ እንደሚችል ተዘግቧል።
ቤቲስ ከባይ በተጨማሪ በውሰት ከሌይስተር ከወሰዱት አዮዜ ፔሬዝ ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል።
ጀርመናዊውን አማካይ የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ግልጥ ያደረጉት ባየርን ሙኒኮች፤ ባርሴሎና ተጫዋቹን ማማለል እንዲያቆም አሳስበዋል።